| 1 | ሳይከካ ተቦካ |
| 2 | ቀና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ |
| 3 | አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል |
| 4 | አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል |
| 5 | ያለ አንድ የላት ጥርስ በዘነዘና ትነቀስ |
| 6 | የምታቦካው የላት የምትጋግረው አማራት |
| 7 | የጅብ ፍቅር እስኪቸግር |
| 8 | አላርፍ ያለች ጣት ስትጠነቁል ትያዛለች |
| 9 | በሬ ከአራጁ ይውላል |
| 10 | በቅሎ ግዙ ግዙ አንድ አሞሌ ጨው ላያግዙ |
| 11 | ዘመድ ከዘመዱ አህያ ከአመዱ |
| 12 | ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል |
| 13 | አይጥ ሞቷን ስትሻ ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ |
| 14 | ከድጡ ወደ ማጡ |
| 15 | የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል |
| 16 | የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ |
| 17 | አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል |
| 18 | በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት |
| 19 | አልሸሹም ዞር አሉ |
| 20 | ታጥቦ ጭቃ |
| 21 | የቆጡን አወርዳለሁ ብላ የብብቷን ጣለች |
| 22 | ለሰው ብሎ ሲያማ ለኔ ብለህ ስማ |
| 23 | ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይከፋሽ |
| 24 | ባጎረስኩት እጄ ምነው መነከሴ |
| 25 | እጸድቅ ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች |
| 26 | ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል |
| 27 | ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ፀሎት |
| 28 | ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም |
| 29 | የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል |
| 30 | አያዘልቅ ፀሎት ለቅስፈት |
| 31 | ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ |
| 32 | ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ |
| 33 | ያልጠረጠረ ተመነጠረ |
| 34 | አዛኝ ቅቤ አንጓች |
| 35 | ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ |
| 36 | ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ |
| 37 | ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል |
| 38 | አህያውን ፈርቶ ዳውላውን |
| 39 | ሴት የላከው ሞት አይፈራም |
| 40 | ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል |
| 41 | ስራ ለሰሪው እሾህ ለአጣሪው |
| 42 | አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ |
| 43 | ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ |
| 44 | አመድ በዱቄት ይስቃል |
| 45 | ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራለትም |
| 46 | የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም |
| 47 | አትሩጥ አንጋጥ |
| 48 | መቀመጥ መቆመጥ |
| 49 | ካለ ፈጣሪ አሟጠሽ ጋግሪ |
| 50 | የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው |
| 51 | ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ |
| 52 | ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ |
| 53 | አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት መጽሀፍ አጥባ ቆየች |
| 54 | የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ |
| 55 | እሱ የከፈተውን ጉሮሮ ሳይዘጋው አያድርም |
| 56 | ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ |
| 57 | አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ |
| 58 | ንገረው ንገረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው |
| 59 | አታግባና የሰው አጥር ዝለል |
| 60 | ከስስታም አንድ ይወድቀው አንድ ይተርፈው |
| 61 | ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት |
| 62 | ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል |
| 63 | አተርፍ ባይ አጉዳይ |
| 64 | አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል |
| 65 | የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ |
| 66 | ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል |
| 67 | ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሀምሳ ሰው ጌጡ |
| 68 | እውነቱን ተናግሮ ካመሹበት ማደር |
| 69 | ድር ቢያብር አንበሳ ያስር |
| 70 | ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል |
| 71 | ከእጅ አይሻል ዶማ |
| 72 | በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ |
| 73 | የአህያ ባል ከጅብ አያስጥል |