| 74 | ከወፈሩ ሰው አይፈሩ |
| 75 | ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት |
| 76 | ሲስሟት ቀርቶ ሲስቧት |
| 77 | ቀድሞ ማን ቢስምሽ ታሞጠሙጫለሽ |
| 78 | እግረ ቀጭን ይሞታል ሲሉ እግረ ወፍራም ይቀድማል |
| 79 | ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል |
| 80 | በቦሃ ላይ ቆረቆር |
| 81 | የቸገረው እርጉዝ ያገባል፣ የባሰበት እመጫት |
| 82 | የአህያ ስጋ አልጋ ሲሉት መሬት |
| 83 | ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም |
| 84 | የደላው ሙቅ ያኝካል |
| 85 | የፈሪ ዱላው ረጅም ነው |
| 86 | የፈሪ በትር ሆድ ይቀትር |
| 87 | ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ ንጣት ይገለው ነበር |
| 88 | ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ |
| 89 | ተንጋለው ቢተፉ ተመልሶ ካፉ |
| 90 | ሰዶ ማሳድድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ |
| 91 | ዞሮ ዞሮ ወደቤት ኖሮ ኖሮ ወደ መሬት |
| 92 | ራሴን ሲበላኝ እግሬን ቢያኩኝ አይገባኝም |
| 93 | የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም |
| 94 | ከዕባብ እንቁላል እርግብ አይፈለፈልም |
| 95 | አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው |
| 96 | ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ |
| 97 | በአንድ ራስ ሁለት ምላስ |
| 98 | ብላ ባለኝ እንዳባቴ በቆመጠኝ |
| 99 | የድሀ ቅንጡ እንጀራ ሲሰጡት ይላል ድልህ አምጡ |
| 100 | ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል |
| 101 | ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል |
| 102 | ወረቀትና ሞኝ የያዘውን አይለቅም |
| 103 | አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ባሰብሽ |
| 104 | ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም |
| 105 | ዘመደ ብዙ ጠላው ቀጭን ነው |
| 106 | ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል |
| 107 | ከድሀ ከመበደር ከባለጸጋ መስረቅ ይቀላል |
| 108 | ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል |
| 109 | ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አያስታውቅም |
| 110 | የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም |
| 111 | አስቀድሞ ነበር መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ይሰራል ድስት ድጦ ማልቀስ |
| 112 | ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም |
| 113 | ጭብጥ ቆሎ ይዘህ ወደ አሻሮ ተጠጋ |
| 114 | ውሀ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው |
| 115 | የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ |
| 116 | ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ |
| 117 | ልጅን ሲወዱ እስከነ ንፍጡ ነው |
| 118 | መልካም ስም ከመልካም ሽቶ ይበልጣል |
| 119 | ሰውና እንጨት ተሰባሪ ነው |
| 120 | ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች |
| 121 | ሰው ጥራ ቢሉት ራሱ መጣ |
| 122 | ምንም ብቀጥን ጠጅ ነኝ |
| 123 | በቅሎን አባትሽ ማነው ቢሏት እናቴ ፈረስ ነች አለች |
| 124 | ቀጥኜ ቢያየኝ ጅማት ለመነኝ |
| 125 | የአዝማሪ ሚስት አልቅሰው ካልነገሯት አይገባትም |
| 126 | ምነው እናቴ እንቁላል ስሰርቅ በቀጣችኝ |
| 127 | ዶሮ ብታልም ጥሬዋን |
| 128 | ዶሮ ጭራ ጭራ መታረጃዋን ታወጣለች |
| 129 | አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል |
| 130 | የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር |
| 131 | ወሬ ቢበዛ በአህያ አይጫንም |
| 132 | ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ |
| 133 | የማያውቁት አገር አይናፍቅም |
| 134 | ዳሩ ሲወረር መሀሉ ዳር ይሆናል |
| 135 | መካሪ የሌለው ንጉስ አንድ አመት አይነግስ |
| 136 | ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ |
| 137 | የአገሩን መሬት በአገሩ በሬ |
| 139 | ታሞ የተነሳ እግዜርን ረሳ |
| 140 | ለጌታም ጌታ አለው |
| 141 | ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል |
| 142 | ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ |
| 143 | ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ |
| 144 | ሰውን ማመን ቀብሮ አለች ቀበሮ |
| 145 | ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም |
| 146 | ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለእዳ አይቀበለውም |
| 147 | ከሞመት መሰንበት |
| 148 | የወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል |
| 149 | አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ |
| 150 | እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች አህያ |
እርማት ወይም ተጨማሪ ምሳሌዎች ካልዎት በኢሜይል አድራሻችን ሊልኩልን ይችላሉ፡፡