| 151 | ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም |
| 152 | በአንድ ራስ ሁለት ምላስ |
| 153 | በሁለት ቢላዋ መብላት |
| 154 | የሽሮ ድንፋታ ከእሳት እስኪወጣ |
| 155 | በለፈለፉ ባፍ ይጠፉ |
| 156 | ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ |
| 157 | ሁለት ሰላምታ አንዱ ለነገር ነው |
| 158 | የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል |
| 159 | የላጭን ልጅ ቅማል በላት |
| 160 | በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ |
| 161 | ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በተኮነንኩኝ |
| 162 | ያልሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል |
| 163 | ለቀባሪው አረዱት |
| 164 | ማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ |
| 165 | ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ |
| 166 | ጅብ በቀደደው ውሻ ይገባል |
| 167 | ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች |
| 168 | ዛፍ ያጣ ጉሬዛ |
| 169 | ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው |
| 170 | አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል |
| 171 | ከልጅ አትጫወት ይወጋሃል በእንጨት |
| 172 | ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ |
| 173 | ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ |
| 174 | ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ |
| 175 | አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም |
| 176 | የዕብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል |
| 177 | ለወሬ የለው ፍሬ |
| 178 | በሽታውን የደበቀ መድሀኒት አይገኝለትም |
| 179 | ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም |
| 180 | ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ |
| 181 | ትለብሰው የላት የምትከናነበው አማራት |
| 182 | የበላችው ያገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታል |
| 183 | እንኳን ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ |
| 184 | በባዳ ቢያኮርፉ: በጨለማ ቢያፈጡ: ምን ሊያመጡ |
እርማት ወይም ተጨማሪ ምሳሌዎች ካልዎት በኢሜይል አድራሻችን ሊልኩልን ይችላሉ፡፡