Wed02222012

Last update04:15:17 PM

Amharic

የአቶ አንዱዓለም አራጌ ደህንነት አደጋ ላይ ነው! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

አሁኑ ጊዜ አቶ አንዱዓለም አራጌ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ይገኛል፡፡ ከአስተማማኝ ምንጮች በተገኘ መረጃ መሠረት የካቲት 7 ቀን 2ዐዐ4 ዓም ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት ገደማ ለህይወቱ የሚያሰጋ ከባድ ድብደባ ተፈጽሞበታል፡፡ ድብደባውን የፈፀመው አቶ አንዱዓለም በታሰረበት ክፍል ውስጥ የሚገኝ ኢባስ አስፋው የሚባል ፍርደኛ ነው፡፡ ይህ ሰው አቶ አንዱዓለም በክፍሉ ውስጥ የግል ጉዳዩን በማከናወን ላይ በነበረበት ጊዜ በአልታወቀ ምክንያት መጀመሪያ  በእርግጫ መትቶ ከጣለው በኋላ በወደቀበት ላይም አሁንም ጫማ በአደረገ እግሩ በስሚንቶ ወለሉ ላይ ደጋግሞ በመርገጥ ነፍሱን እስከመሳት የሚያደርስ ድብደባ እንደፈፀመበት ተገልፆልናል፡፡ ህይወቱ የተረፈውም በክፍሉ ውስጥ በነበሩ ታራሚዎች ገላጋይነት መሆኑም ታውቋል፡፡ Read full text

‹‹ለኢትዮጵያ መንግሥት ከህንድና ከቻይና መበደር የሚቀልበት ምክንያት ብድሮቹ ሲሰጡ የማይነሱ ጥያቄዎች ስላሉ ነው››

አቶ ሙሼ ሰሙ፣ የኢዴፓ ፓርቲ ፕሬዚዳንትና የባንክ ባለሙያ

ባለፈው ዓመት የነበረው የመንግሥት የውጭ ብድር 134 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ይህ አኅዝ በዚህ ዓመት ወደ 200 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሏል፡፡

የአገር ውስጥ ብድርም ወደ 60 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሏል፡፡ በመንግሥት የሚሠሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶችም ሲጀመሩ ብድሩ ወደ 500 ቢሊዮን ብር ከፍ ይላል የሚል ግምት አለ፡፡ መንግሥት በአሁኑ ወቅት እየተበደረ ያለው ከፍተኛ የወለድ መጠን ካላቸው የቻይናና የህንድ ባንኮች ሲሆን፣ በርካታ ጥያቄዎችን እያስነሳ ነው፡፡ በዚህና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚዳንትና የባንክ ባለሙያ ከሆኑት አቶ ሙሼ ሰሙ ጋር ዘካሪያስ ስንታየሁ ቆይታ አድርጓል፡፡ Click here to read full text (Reporter)

የአርባ ዓመት የትግል ጉዞ በ”የሁለት ምርጫዎች ወግ”

ሙሼ ሰሙ   የኢዴፓ ሊ/መንበር

ሰዎች ዘርዘር አድርገው ካልጻፉና ካልተናገሩ በማንኛውም ጉዳይ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለመረዳት ያዳግታል፡፡ በኢህአዴግ ጎራ እንደተለመደው ተቃዋሚዎችን በተቀጥላ ስምና በጥቅሉ ጠባብ፣ ትምክህተኛ… እያሉ ከመጥራት አባዜ ተላቆ በመጸሐፍ መልክ ለመተቸትም ሆነ ለመተንተን “የሁለት ምርጫዎች ወግ” አንድ እርምጃ ወደፊት የተራመደ ነው፡፡ አንድ አንድ ቦታዎች ላይ የኢህአዴግን ድክመቶች በድፍረትና በመረጃ እያጣቀሱ ለመናዘዝ የተደረገውም ሙከራ ከተለመደው የሰበብና ምክንያት ፍለጋ ፖለቲካ ወጣ ያለ በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ መጽሐፉ ከላይ ከጠቀስኳቸው መልካም መነሻዎች ውጭ በአጠቃላይ በመረጃ አቀራረብ፣ በሁነቶች አሰላለፍ፣ በመቼት አደራደር ላይ እጅግ ብዙ የሚቀረው ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡የሁለት ምርጫዎች ወግን ስናጤን ከግምት ውስጥ መግባት የሚገባው መሰረታዊ ነጥብ አለ፡፡ Click here to read full text (Addis Admas)

ስለ ሊዝ አዋጁ በቴሌቭዥን የተደረገዉ ክርክርና ምላሽ ለመስጠት ያልተቻለው ጥያቄ

ከመስፍን መንግስቱ (የግል አስተያየት)

(pdf) በህዳር 15 እና 16 ምሽቶች የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቅርቡ በወጣዉ የሊዝ አዋጅ ዙሪያ መንግስትንና ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን አከራክሯል፡፡ ክርክሩ በመደንበሽና መሻገት ሂደት ውስጥ ፈጥኖ እየተጓዘ ለሚገኘዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትንሽም ቢሆን የመነቃቃት ጠብታ ሳይሆን አልቀረም፡፡ ይህ ክርክር ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የአገራዊ የፖለቲካ ልዩነት መንስኤ ሆነዉ ከቆዩ ሀሳቦች መካከል በመሬት ይዞታ ዙሪያ ኢህአዴግንና ተቃዋሚዎችን እንደገና አፋልሟል፡፡ ይህ አጭር ጹሁፍ በክርክሩ ላይ የቀረቡት ሁለቱ የኢህአዴግ ባለሥልጣኖች አፅንኦት ስጥተዉ ካቀረቡ ሃሳቦች አንጻር በአንዳንዶቹ ላይ የቀረበ አስተያየት ነዉ፡፡

የአቶ በረከት ስምኦን መጽሐፍ

ታሪኩንም እንደ ምርጫዉ
ከመስፍን መንግስቱ

(pdf) ሰሞኑን አቶ በረከት ስምኦን የጻፉት መጽሀፍ የመወያያ ርዕስ ሆኖ ከርሟል፡፡ መጽሐፉን ካነበብኩ በኋላ አስተየያት መስጠትን የግድ የሚያደርግ ሆኖ አገኘሁት፡፡ በመጽሀፉ ስሜቴን እጅግ አድርገዉ ወዳነሳሱብኝ ዝርዝር ጉዳዮች ከመግባቴ በፊት አንድ ጠቅለል ያለ ሀሳብ ማንሳት የግድ ሊለኝ ነዉ፡፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብዙ ፖለቲካዊ መጽሐፎች እየተጻፉ ናቸዉ፡፡ፖለቲካዊ መጽሐፎች ብዙ ጊዜ እየተጻፉ የቆዩ ቢሆኑም ከብዛታቸዉ በተጨማሪ የጸሀፊዎች ማንነት ትኩረትን የሚስብ ነዉ፡፡ ከቀድሞ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማሪያም ጋር የተደረገዉ ቃለ ምልልስ ከታተመ በኋላ ሌላኛዉ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳም ተመሳሳይ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡

Related Links